ምሳሌ 25:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ማር መብላት መልካም አይደለም፥ ክቡር ነገሮችን መፈለግ ግን የሚያስከብር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመጠን በላይ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤ የራስንም ክብር መሻት አያስከብርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ማር. መብላት መልካም አይደለም፤ እንዲሁም ከሰው ክብርን ለማግኘት መፈለግ አያስከብርም። |
በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።
ከራስ ወዳድነት ወይም ከትምክሕት የተነሣ አንድም ነገር አታድርጉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በትሕትና ባልንጀራውን ከራሱ ይልቅ እንደሚሻል አድርጎ ይቁጠር፤