Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 25:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በኀጥእ ፊት የሚወድቅ ጻድቅ እንደደፈረሰ ምንጭና እንደ ተበከለ ኩሬ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ለክፉ ሰው የሚንበረከክ ጻድቅ፣ እንደ ደፈረሰ ምንጭ ወይም እንደ ተበከለ የጕድጓድ ውሃ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የክፉን ሰው ጠባይ የሚወርስ ደግ ሰው የደፈረሰን ምንጭ ወይም የተመረዘን ኲሬ ይመስላል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 25:26
10 Referencias Cruzadas  

ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ በእጅጉ ተደነቅሁ።


እነዚያም ጌታን ኢየሱስንና ነቢያትን ገደሉ፤ እኛንም ደግሞ አሳደዱ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙም፤ ሰዎችንም ሁሉ ይቃወማሉ፤


ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ገደላችሁትም።”


የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።


ቃየንም ወንድሙን አቤልን፥ “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳም ሳሉ፥ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios