በቀና ነገር የሚመልስ በፍቅር ይሰማል።
እውነተኛ መልስ መስጠት፣ ከንፈርን እንደ መሳም ነው።
ትክክለኛ መልስ የሚሰጥ ሰው እንደ ልብ ወዳጅ ይቈጠራል።
ሰይፈ መዓቱ ብትሳል ግን ከዘሮቹ ጋር ሰውን ታጠፋለች፤ የሰውንም አጥንት ትቈረጥማለች።
የቅንነት ቃል እንዴት ኃይለኛ ነው! የእናንተ ሙግት ግን ምን ይገሥጻል?
ሰው በአፉ መልስ ደስ ይለዋል፥ ቃልም በጊዜው ምንኛ መልካም ነው!
የልብ መዘጋጀት ከሰው ነው፥ የምላስ መልስ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።
የሚዘልፉት ግን ደስታ ይሆንላቸዋል፥ በላያቸውም መልካም በረከት ትመጣላቸዋለች።
ሥራህን በውጭ አሰናዳ፥ ለራስህ በእርሻ ውስጥ አዘጋጀው፥ ከዚያም በኋላ ቤትህን ሥራ።