ጣፋጩ መብል አይመርህ የሐሰት እንጀራ ነውና።
የርሱ ጣፋጭ መብል አያስጐምጅህ፤ ምግቡ አታላይ ነውና።
ምናልባት ሊታዘብህ ስለሚችል የሚያቀርብልህን መልካም ምግብ ተስገብግበህ አትብላ።
ብትሳሳ ግን ምግቡን አትውደድ እርሱ የሐሰት እንጀራ ነውና።
ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፅን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለክፋት ምክንያት እንዳልሰጥ፥ ከድግሳቸውም አልቅመስ።
የንፉግን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ፥
“ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር፥ ስለ ኑሮም ማሰብ እንዳይዝል፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤
ስለ ቀድሞ አኗኗሯችሁም፥ በሚያታልል ምኞቱ የጎደፈውንና የተበላሸውን፥ አሮጌ ሰው አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤