የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባሏ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባርያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው።
ምሳሌ 22:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መክፈል ባትችል፥ ለምን የምትተኛበት አልጋ ይወሰድብሃል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትከፍለው ካጣህ፣ የምትተኛበት ዐልጋ ከሥርህ ይወሰድብሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መክፈል ባትችል የምትተኛበት አልጋ እንኳ ሳይቀር ያለህ ንብረት ሁሉ ይወስድብሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምትከፍለው ባይኖርህ፥ ምንጣፍህን ከጎንህ ይወስዱብሃልና። |