የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ግን ለመጉደል ይቸኩላል።
የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤ ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።
በጥንቃቄ በወጣ ዕቅድ የሚሠራ ሥራ ትርፍ ያስገኛል፤ ያለ ዕቅድ በችኰላ የሚሠራ ሥራ ግን ያደኸያል።
የትጉህ ዐሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።
የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፥ የትጉ እጅ ግን ሀብታም ታደርጋለች።
የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።
ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፥ ቁጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።
በመጀመሪያ ፈጥኖ የተከማቸ ርስት ፍጻሜው አይባረክም።
ምቀኛ ሰው ሀብታም ለመሆን ይጣደፋል ችጋርም እንደሚመጣበት አያውቅም።
በችኮላ የሚናገረውን ሰው አየኸውን? ከእርሱ ይልቅ ለሰነፍ ተስፋ አለው።
የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።