ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።
ሰነፍን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤ እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።
መሥራት የማይፈልግ ሰነፍ ሰው ራሱን የገደለ ያኽል ይቈጠራል።
ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ምንም ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።
የትጉ እጅ ትገዛለች፥ የታካች እጅ ግን ትገብራለች።
ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፥ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።
የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።
የታካች መንገድ እንደ እሾህ አጥር ናት፥ የጻድቃን መንገድ ግን የተደላደለች ናት።
ታካች ሰው እጁን በወጭቱ ያጠልቃታል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።
ታካች ሰው በብርድ ምክንያት አያርስም፥ ስለዚህ በመከር ይለምናል፥ ምንም አያገኝም።
ሰነፍ ሰው፦ “ውጪ አንበሳ አለ፤ ብወጣ፥ በመንገዱ ላይ እሞታለሁ” ይላል።
ሰነፍ ሰው፦ “አንበሳ በመንገድ ላይ አለ፥ አንበሳ በጎዳናዎች ላይ አለ” ይላል።
ሰነፍ ሰው በጥበብ ከሚመልሱ ከሰባት ሰዎች ይልቅ ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል።
ጌታውም እንዲህ ሲል መለሰለት ‘አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባርያ፥ ካልዘራሁበት እንደማጭድ ካልበተንሁበትም እንደምሰበስብ ታውቃለህን?
ወደ ኢያሱም ተመልሰው እንዲህ አሉት፦ “ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይውጣ፤ ጥቂቶች ናቸውና ሕዝቡ ሁሉ ወደዚያ ለመሄድ አይድከም።”