La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 21:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጻድቅ ስለ ኀጥእ ቤት ያስባል፥ ኀጥኣንም ለጥፋት እንደ ተገለበጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጻድቁ የክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጻድቁ አምላክ በክፉዎች ቤት የሚደረገውን ሁሉ ይመለከታል። ክፉዎችንም አሸቀንጥሮ በመጣል ያጠፋቸዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የክፉዎች ልብ ጽድቅን አያውቅም፥ ክፋትም ኃጥአንን ያከፋቸዋል።

Ver Capítulo



ምሳሌ 21:12
20 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፥ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።


አላዋቂውን ሰው ሥር ሰድዶ አየሁት፥ ድንገትም መኖሪያውን ረገምሁ።


ቤቱን ይደገፈዋል፥ ነገር ግን አይቆምለትም፥ ይይዘውማል፥ አይጸናለትም።


ጠቢብ ማነው? ይህንን ይፈጽም፥ እርሱ የጌታንም ጽኑ ፍቅር ይገነዘባል።


ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዓመፃን ወደድህ።


በመንገዱ ያለ ነውር የሚሄደውን ጽድቅ ይጠብቀዋል፥ ኃጢአት ግን ኃጢአተኛውን ይጥለዋል።


የኀጥኣን ቤት ይፈርሳል፥ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።


ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፥ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።


ክፉ ሰዎች ሥልጣን ሲይዙ ሕግ መጣስ ይበዛል፥ ጻድቃን ግን ውደቀታቸውን ያያሉ።


ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።


“ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ እንዲሁ ገለባበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።


እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በአብዛኞቹ ደስ አልተሰኘም፤ እነርሱ ምድረ በዳ ወድቀው ቀርተዋልና።