ምሳሌ 20:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጎበዛዝት ክብር ጉልበታቸው ናት፥ የሽማግሌዎችም ጌጥ ሽበት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጕልማሶች ክብር ብርታታቸው፣ የሽማግሌዎችም ሞገስ ሽበታቸው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወጣቶች መመኪያ ብርታታቸው ነው፤ የሽማግሌዎችም መከበሪያ ሽበታቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጐልማሶች ጌጣቸው ጥበብ ነው። ለሽማግሌዎችም ክብራቸው ሽበት ነው። |
ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችሁታልና ጽፌላችኋለሁ። አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችሁታልና ጽፌላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በውስጣችሁ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ ጽፌላችኋለሁ።