ምሳሌ 20:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐሰት እንጀራ ለሰው የጣፈጠ ነው፥ ከዚያ በኋላ ግን አፉ ጭንጫ ይሞላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ይጣፍጠዋል፤ በመጨረሻ ግን አፉን ኰረት ሞልቶት ያገኘዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማጭበርበር የምታገኘው ነገር እንደ ጣፋጭ ምግብ ሊያስደስትህ ይችላል፤ ነገር ግን ውሎ ሲያድር በአፍ ውስጥ እንደ አሸዋ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐሰት እንጀራ ለሰው የጣፈጠ ነው፤ ከዚህ በኋላ ግን አፉ ጭንጫ ይሞላል። |
አንተ ጐበዝ፥ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።