ምሳሌ 20:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕቃ የሚገዛ “አይረባም አይረባም” ብሎ ያራክሳል፥ ገዝቶ ሲመለስ ግን በገዛው ዕቃ ይኩራራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕቃ የሚገዛ፣ “የማይረባ ነው፤ የማይረባ ነው” ብሎ ያራክሳል፤ ሲመለስ ግን በግዥው ይኵራራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገዢ ዘወትር መጥፎ ነው እያለ ዕቃን ያራክሳል፤ ገዝቶ ከሄደ በኋላ ግን “በርካሽ ገዛሁ” እያለ ይመካል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚገዛ ሰው፦ “ክፉ ነው፥ ክፉ ነው” ይላል፤ በሄደ ጊዜ ግን ይመካል። |
አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።