መንገዳቸውን የሚጠመዝዙ አካሄዳቸውንም የሚያጣምሙ ናቸው፥
መንገዳቸው ጠማማ፣ በአካሄዳቸው ጠመዝማዞች ናቸው።
እነርሱ እምነት የማይጣልባቸውና ጠማሞች ናቸው።
መንገዳቸው ጐጻጕጽ፥ አካሄዳቸው ጠማማ ለሆኑ ወዮላቸው!
ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።
በቅን የሚሄድ ሰው ጌታን ይፈራል፥ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይንቀዋል።
የበደለኛ መንገድ የጠመመች ናት፥ የንጹሕ ሥራ ግን የቀና ነው።
የአፌ ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው፥ በውስጣቸውም ምንም ጠማማና ጠመዝማዛ ነገር የለም።
የሰላምን መንገድ አያውቁም፤ በአካሄዳቸውም ፍትህ የለም፤ መንገዳቸውን አጣመዋል፥ የሚሄድባትም ሁሉ ሰላምን አያውቅም።
በእርሱ ፊት ክፋት ፈጽመዋል፤ ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም፤ ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው።
በዚህም በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ሆናችሁ በዚህ ዓለም እንደ ከዋክብት የምታበሩ፥ ያለ ነቀፋ የዋሆችና ነውርም የሌለባችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ፤