ኃጢአትን የሚከድን ሰው ፍቅርን ይሻል፥ ነገርን የሚደጋግም ግን የተማመኑትን ወዳጆቹን ይለያያል።
በደልን የሚሸፍን ፍቅርን ያዳብራል፤ ነገርን የሚደጋግም ግን የልብ ወዳጆችን ይለያያል።
የበደለን ሰው ይቅር የሚል ወዳጅነትን ያጸናል፤ በደልን መላልሶ የሚናገር ሰው ግን የቅርብ ወዳጆቹን ያጣል።
በደሉን የሚሰውር ሰው ዕርቅን ይሻል፤ በደሉን መሰወር የሚጠላ ግን ቤተሰቦችንና ወዳጆችን ይለያያል።
የዳዊት ትምህርት። መተላለፉ ይቅር የተባለችለት፥ ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው።
ጥላቻ ክርክርን ታስነሣለች፥ ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ትከድናለች።
ጠማማ ሰው ጥልን ይዘራል፥ ጆሮ ጠቢ ሰው የተማመኑትን ወዳጆች ይለያያል።
መቶ ግርፋት በሰነፍ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሣጽ በአስተዋይ ሰው ጠልቆ ወደ ልቡ ይገባል።
ፍቅር ይታገሳል፤ ቸርነትንም ያደርጋል። ፍቅር አይቀናም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤
ይህን ይወቅ፤ ኀጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ ሰው ነፍሱን ከሞት ያድንለታል፤ ብዙ ኃጢአቱንም ይቅርታ ያስገኝለታል።
ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።