ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፥ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።
ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኀኒት ነው፤ የተሰበረ መንፈስ ግን ዐጥንትን ያደርቃል።
ደስተኛነት ለልብ መልካም መድኃኒት ነው፤ የመንፈስ ሐዘንተኛ መሆን ግን አጥንትን ይሰብራል።
ደስ ያላት ልብ ፈውስን ታገኛለች፤ ኀዘንተኛ ሰው ግን አጥንቱን ያደርቃል።
እንደ ውኃ ፈሰስሁ፥ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ፥ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ።
ሰውን የልቡ ኀዘን ያዋርደዋል፥ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።
ደስ ያለው ልብ ፊትን ያበራል፥ በልብ ኀዘን ግን ነፍስ ትሰበራለች።
ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፥ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።
የሰው ነፍስ ሕመሙን ይታገሣል፥ የተቀጠቀጠን መንፈስ ግን ማን ያጠንክረዋል?
“ሳቅን፦ ዕብደት፥ ደስታንም፦ ዋጋ ቢስ” አልሁት።
ከልክ በላይ አዝኖ ተስፋ እንዳይቆርጥ ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባችኋል።
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ወደ መዳን ለሚያደርስ ንስሓ ያበቃል፤ ጸጸትም የለበትም፤ ዓለማዊው ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።