መቶ ግርፋት በሰነፍ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሣጽ በአስተዋይ ሰው ጠልቆ ወደ ልቡ ይገባል።
መቶ ግርፋት ሞኝን ከሚሰማው ይልቅ፣ ተግሣጽ ለአስተዋይ ጠልቆ ይሰማል።
ሞኝ መቶ ጊዜ ተገርፎ ከሚማረው ይልቅ አስተዋይ ሰው ከአንድ ጊዜ በማይበልጥ ተግሣጽ የሚማረው ይበልጣል።
ትምክሕት የአስተዋይ ሰው ልቡናን ያሳዝነዋል፥ አላዋቂ ግን ተገርፎ ግርፋቱ አይታወቀውም፥
ጻድቅ በጽኑ ፍቅር ይገሥጸኝ፥ ይዝለፈኝም፥ የክፉ ሰው ዘይት ግን ራሴን አይቀባ፥ ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና።
ባለ አእምሮ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፥ ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም።
ሰነፍ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚቀበል ግን አእምሮው የበዛ ነው።
ክፉ ሰው ዓመፃን ብቻ ይሻል፥ ስለዚህ ጨካኝ መልአክ ይላክበታል።
ኃጢአትን የሚከድን ሰው ፍቅርን ይሻል፥ ነገርን የሚደጋግም ግን የተማመኑትን ወዳጆቹን ይለያያል።
ፌዘኛ ብትገርፈው አላዋቂ ብልሃተኛ ይሆናል፥ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው እውቀትን ያገኛል።
ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ሞኝነቱ ከእርሱ አይርቅም።
አገልጋይ በቃል ብቻ አይገሠጽም፥ ቢያስተውል እንኳ አይመልስምና።
እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።