ምሳሌ 16:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሥ ፊት ሲፈካ ብርሃን አለ፥ መልካም ፈቃዱም እንደ በልግ ዝናብ ደመና ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ፊት ሲፈካ ሕይወት አለ፤ በጎነቱም ዝናብ እንዳዘለ የበልግ ደመና ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሥ ፈገግታ ሕይወት ነው፤ ከእርሱም ተወዳጅነትን ማግኘት እንደ በልግ ዝናብ ልምላሜን ይሰጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሥ ልጅ እንደ ሕይወት ብርሃን ነው፥ በማያስደስቱትም ዘንድ የማታ ደመና ነው። |
እኛም እንወቅ፤ ጌታን ለማወቅ እንትጋ፤ እንደ ንጋትም መገለጡ እርግጥ ነው፤ እንደ ዝናብ ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ በልግ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
የበልግ ዝናብ እንዲሰጣች ጌታን ለምኑ፤ መብረቁን ደመና የሚያደርግ ጌታ፥ ያደርጋል፥ እርሱም ለእያንዳንዱ የምድር ተክል የሚሆን ዝናብ ይሰጣል።