በድሆች እርሻ ላይ ብዙ ሲሳይ አለ፥ ከፍርድ መጉደል የተነሣ ግን ይጠፋል።
የድኾች ዕርሻ የተትረፈረፈ ምርት ያስገኛል፤ የፍትሕ መጓደል ግን ጠራርጎ ይወስደዋል።
የድኻ እርሻ የተትረፈረፈ ምርትን ሊያስገኝ ይችል ይሆናል። ከፍርድ መጓደል የተነሣ ግን ይጠፋል።
ጻድቃን ለብዙ ዓመት በብልጽግና ይኖራሉ፤ ዐመፀኞች ግን ፈጥነው ይጠፋሉ።
ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ ነገሩንም በቀና መንገድ ይፈጽማል።
መሬቱን የሚቆፍር ሰው እንጀራ ይጠግባል፥ ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን ማስተዋል የተሣነው ነው።
የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም እንደ እጁ ሥራ ዋጋውን ይቀበላል።
በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።
ምድሩን የሚያርስ እንጀራ ይጠግባል፥ የማይረቡ ሰዎችን የሚከተል ግን ድህነት ይሞላበታል።
ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፥ ሀብትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደ የማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን አንገት ይስበሩት፤