ምሳሌ 13:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጥፎ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል፥ የታመነ መልእክተኛ ግን ፈውስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ መልእክተኛ መከራ ውስጥ ይገባል፤ ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስን ያመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ መልእክተኛ ችግርን ያመጣል፤ ታማኝ መልእክተኛ ግን ሰላምን ያስገኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፍ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል፤ ብልህ መልእክተኛ ግን ራሱን ያድናል። |
እኔ ኃጢአተኛውን፦ ሞትን ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ ካላስጠነቀቅኸው፥ ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን አስጠንቅቀህ ካልነገርኸው፥ ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት።
የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚነግዱ እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።
ስለዚህ እግዚአብሔር ጥሪውን የሚያቀርበው በእኛ በኩል በመሆኑ፥ እኛ ለክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ስለ ክርስቶስ ሆነን “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን።