ምሳሌ 10:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆምጣጤ ጥርስን፥ ጢስም ዓይንን እንደሚጐዳ፥ ሰነፍም ለላኩት እንዲሁ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሖምጣጤ ጥርስን፣ ጢስ ዐይንን እንደሚጐዳ፣ ሰነፍም ለሚልኩት እንዲሁ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆምጣጤ ጥርስን፥ ጢስ ዐይንን እንደሚጐዳ ሰነፍ ሰውም ለአሠሪው እንደዚሁ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጨርቋ ለጥርስ፥ ጢስም ለዐይን ጎጂ እንደ ሆነ፥ ኀጢአትም ለሚሠሯት እንዲሁ ናት። |
እነርሱም፦ “ለራስህ ቁም፥ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና ወደ እኔ አትቅረብ” ይላሉ፤ እነዚህ ቀኑንም ሁሉ የምትነድድ እሳት፥ በአፍንጫዬ ስር የምታልፍ ጢስ ናቸው።