Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 12:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ጌታን አገልግሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሳትታክቱ የጋለ መንፈስን ተከትላችሁ ጌታን አገልግሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ለሥራ ከመ​ት​ጋት አት​ስ​ነፉ፤ በመ​ን​ፈስ ሕያ​ዋን ሁኑ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 12:11
33 Referencias Cruzadas  

እርሱ የጌታን መንገድ የተማረ ነበረ፤ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር።


ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።


ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤


የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።


ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ ለወንድማማች እውነተኛ ፍቅር፥ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


ከሕገ ወጥነት ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።


ሆምጣጤ ጥርስን፥ ጢስም ዓይንን እንደሚጐዳ፥ ሰነፍም ለላኩት እንዲሁ ነው።


በሥራው ብልህ ሰው ትመለከታለህን? በነገሥታት ፊት ያገለግላል፥ በተራ ሰዎችም ፊት ሊያገለግል አይቆምም።


በሥራው ታካች የሚሆን የሀብት አጥፊ ወንድም ነው።


እርሱም አላቸው፦ “ሰልችታችኋል፥ ሰልችታችኋል፤ ስለዚህም፦ ‘እንሂድ ለጌታም እንሠዋ’ ትላላችሁ።


ከዚህም ጎን ለጎን ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ ፈቶችም ብቻ ሳይሆኑ የማይገባቸውን እየተናገሩ ሰውን የሚያሙና በነገር ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።


ጉበኞቹ ዕውሮች ናቸው፥ ሁሉም እውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።


ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።


ጌቶች ሆይ! እናንተ ደግሞ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና ባርያዎቻችሁን በጽድቅና በቅንነት ተመልከቱአቸው።


ባርያ ሆኖ ሳላ በጌታ የተጠራ የጌታ ነጻ ነውና፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ ሳለ የተጠራ የክርስቶስ ባርያ ነው።


ጌታውም እንዲህ ሲል መለሰለት ‘አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባርያ፥ ካልዘራሁበት እንደማጭድ ካልበተንሁበትም እንደምሰበስብ ታውቃለህን?


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።


ገና ሳይነጋ ትነሣለች ለቤትዋም ሰዎች ምግባቸውን፥ ለአገልጋዮችዋም ሥራ ትሰጣለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios