ምሳሌ 1:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚሰማኝ ግን ተረጋግቶ ይቀመጣል፥ ከክፉም ሥጋት ያርፋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያዳምጠኝ ሁሉ ግን በሰላም ይኖራል፤ ክፉን ሳይፈራ ያለ ሥጋት ይቀመጣል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን የሚሰማ ግን ለሕይወቱ ዋስትና ይኖረዋል፤ ምንም የሚያስፈራው ነገር ሳይደርስበት በሰላም ይኖራል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሰማኝ ግን በተስፋ ይኖራል፥ ከክፉም ሁሉ ያለ ድንጋጤ ያርፋል።” |
ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆ ከደመናው ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የተወደደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።