ምሳሌ 1:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥ ሞኞችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አላዋቂዎችን ስድነታቸው ይገድላቸዋል፤ ሞኞችንም መታለላቸው ያጠፋቸዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀት የጐደላቸው ሰዎች ከጥበብ በመራቃቸው ምክንያት ይሞታሉ፤ ሞኞችም ከቸልተኛነታቸው የተነሣ ይጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላዋቂዎችን አለመመለሳቸው ትገድላቸዋለችና፥ ሰነፎችንም ምርመራቸው ትገድላቸዋለች። |
እኔ ደግሞ የተሳለቀባቸውን እመርጣለሁ፥ የፈሩትንም ነገር አመጣባቸዋለሁ። ምክንያቱም በፊቴ ክፉ ነገርን አድርገዋል፥ ያልወደድሁትንም መርጠው በጠራኋቸው ጊዜ አልመለሱልኝም፤ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝም።
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላይ ሲያስረዳቸው እምቢ ያሉት ካላመለጡ፥ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ፈቀቅ የምንል እኛ እንዴት እናመልጣለን?