አብድዩ 1:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአብድዩ ራእይ። ጌታ አምላክ ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከጌታ መልእክት ሰምተናል፥ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በጦርነት እንነሣ ብሏል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፤ መልእክተኛው ወደ አሕዛብ ተልኮ እንዲህ ብሏል፤ “ተነሡ፤ እርሷን ለመውጋት እንውጣ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብድዩ ያየው ራእይ፦ እግዚአብሔር አምላክ ኤዶምን በተመለከተ አብድዩን ልኮአል፤ የሰማነውም የእግዚአብሔር መልእክት፦ “እኔ እግዚአብሔር በኤዶም ላይ አደጋ እንዲጥሉ በማዘዝ ወደ ሕዝቦች መልእክተኛ ልኬአለሁ!” የሚል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማትን ሰማሁ፤ ከባቢን ወደ አሕዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላይዋም እንነሣና እንውጋት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምተናል፥ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በሰልፍ እንነሣ ብሎአል። |
በምድሪቱም ከሚሰማው ወሬ የተነሣ ልባችሁ የዛለ አይሁን አትፍሩም፤ በአንዱም ዓመት አንድ ወሬ፥ በሚቀጥለውም ዓመት ሌላ ወሬ ይመጣል፥ በምድሪቱም ላይ ዓመጽ ይሆናል፥ ገዢም በገዢ ላይ ይነሣል።
ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፤ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጡ፤ ንጉሣቸው በፊታቸው ሄዷል፥ ጌታም በራሳቸው ላይ ነው።