እናንተም፦ ‘ለጌታ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፥ በግብጽ በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነበት ነው’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጎነበሱ ሰገዱም።
ዘኍል 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚያም ሰዎች እርሱን እንዲህ አሉት፦ “የሞተውን ሰው ሬሳ በመነንካት ብንረክስም እንኳ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል የጌታን ቁርባን በተወሰነለት ጊዜ እንዳናቀርብ ለምን እንከለከላለን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴን፣ “በሬሳ ምክንያት ረክሰናል፤ ታዲያ የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነን በተወሰነው ጊዜ እንዳናቀርብ ለምን እንከለከላለን?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኛ በድን በመንካታችን ረክሰናል፤ ነገር ግን ከቀሩት እስራኤላውያን ተለይተን በወቅቱ ለእግዚአብሔር መባ እንዳናቀርብ ስለምን እንከለከላለን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ወደ ሙሴና ወደ አሮን ቀረቡ። እነዚያም ሰዎች “እኛ በሰውነታችን ርኵሰት ያለብን ሰዎች ነን፤ በእስራኤል ልጆች መካከል በጊዜው ቍርባን ለእግዚአብሔር እንዳናቀርብ ስለ ምን እንከለከላለን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያም ሰዎች፦ በሞተ ሰው ሬሳ ረክሰናል፤ በእስራኤል ልጆች መካከል በጊዜው ቍርባን ለእግዚአብሔር እንዳናቀርብ ስለ ምን እንከለከላለን? አሉት። |
እናንተም፦ ‘ለጌታ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፥ በግብጽ በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነበት ነው’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጎነበሱ ሰገዱም።
የሞተ ሰው ሬሳን በመንካት የረከሱ ሰዎችም ነበሩ፥ ስለዚህም በዚያ ቀን የፋሲካን በዓል ለማክበር አልቻሉም ነበር። በዚያም ቀን በሙሴና በአሮን ፊት ቀረቡ።