ዘኍል 9:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሙሴ ፋሲካን እንዲያከብሩ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሙሴ የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ ለሕዝቡ ነገራቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ፋሲካን ያደርጉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ፋሲካን ያደርጉ ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ተናገራቸው። |
በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ የፋሲካን በዓል አከበሩ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ።