La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 5:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሴቲቱንም እንዲህ ብሎ ካህኑ ያምላታል፦ ‘ከአንቺ ጋር ሌላ ወንድ ካልተኛ፥ በባልሽም ሥልጣን ሥር እየነበርሽ ራስሽን ለማርከስ ዘወር ካላልሽ፥ እርግማንን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውኃ የተጠበቅሽ ሁኚ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህኑም ሴትዮዋን ያስምላታል፤ እንዲህም ይላታል፤ “ሌላ ወንድ ዐብሮሽ ካልተኛ፣ በትዳር ላይ ሆነሽ ወደ ርኩሰት ካላዘነበልሽ ይህ ርግማን የሚያመጣ መራራ ውሃ ጕዳት አያድርስብሽ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም ካህኑ እንዲህ ብሎ ያስምላት፦ ከባልሽ ጋር እያለሽ ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር የተኛ ባይሆን፥ ራስሽንም ባታረክሺ ርግማን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውሃ ነጻ ሁኚ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ካህ​ኑም ያም​ላ​ታል፤ ሴቲ​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ታል፦ ሌላ ወንድ አል​ተ​ኛሽ፥ ባል​ሽ​ንም አል​ተ​ውሽ፥ ራስ​ሽ​ንም አላ​ረ​ከ​ስሽ እንደ ሆነ፥ ርግ​ማ​ንን ከሚ​ያ​መጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ካህኑም ያምላታል፥ ሴቲቱንም እንዲህ ይላታል፦ ሌላ ወንድ አልተኛሽ፥ ባልሽንም አልተውሽ፥ ራስሽንም አላረከስሽ እንደ ሆነ፥ እርግማንን ከሚያመጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤

Ver Capítulo



ዘኍል 5:19
5 Referencias Cruzadas  

“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የማንኛውም ሰው ሚስት እርሱን ትታ ፈቀቅ ብትል፥ ለእርሱም ፍጹም ታማኝ ባትሆን፥


ካህኑም ሴቲቱን በጌታ ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም የተሠራ ጠጉር ይፈታል፥ በእጅዋም የመታሰቢያ የእህል ቁርባን የሆነውን የቅንዓት የእህል ቁርባን ያኖራል፤ ካህኑም እርግማንን የሚያመጣውን መራራ ውኃ በእጁ ይይዛል።


ይልቁንም ሴቲቱ ሳትረክስ ንጹሕ ብትሆን ከእርግማን የተጠበቀች ትሆናለች፥ ልጅንም መፀነስ ትችላች።


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህኑም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ከሆንህ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ” አለው።


ያገባች ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ በሕግ ታስራለችና፤ ባሏ ቢሞት ግን ከባል ሕግ ተፈትታለች።