La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእርሱም ላይ የሚገለገሉባቸውን የመሠውያውን ዕቃዎች ሁሉ፥ ጀሞዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ጐድጓዳ ሳሕኖቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም ላይ የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ለመሠዊያው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች በሙሉ፣ የእሳት ማንደጃዎቹን፣ ሜንጦዎቹን፣ የእሳት መጫሪያዎቹንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን በላዩ ላይ ያድርጉ፤ በእነዚህም ላይ የአቆስጣ ቍርበት መሸፈኛ አልብሰው መሎጊያዎቹን በየቦታቸው ያስገቡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመሠዊያው ላይ ለማገልገል የሚጠቅሙትን ዕቃዎች፥ ማለትም ማንደጃዎችን፥ ሜንጦዎችን፥ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ያስቀምጡበት፤ የተለፋውንም ስስ ቊርበት በላዩ ደርበው መሎጊያዎችን ያስገቡበት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ዕቃ​ውን ሁሉ፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ መክ​ደ​ኛ​ዎ​ቹ​ንም፥ ያመድ ማፍ​ሰ​ሻ​ዎ​ቹን፥ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ያስ​ቀ​ም​ጡ​በት፤ በእ​ር​ሱም የአ​ቆ​ስ​ጣን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይዘ​ርጉ፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ። ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ወስ​ደው ማስ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ው​ንና ማስ​ቀ​መ​ጫ​ውን ይሸ​ፍ​ኑት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣው ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስ​ጥም አድ​ር​ገው በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ዎቹ ላይ ያኑ​ሩት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሚያገለግሉበትን ዕቃውን ሁሉ፥ ማንደጃዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ድስቶቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።

Ver Capítulo



ዘኍል 4:14
7 Referencias Cruzadas  

ሰሎሞንም በጌታ ቤት የነበረውን ዕቃ ሁሉ፥ የወርቁንም መሠዊያ፥ የተቀደሰውንም ኅብስት የሚቀመጥባቸውን ገበታዎች ሠራ፤


“ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ሥራ፤ መሠዊያው አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ይሁን።


አመድ የሚጠራቀምባቸውን ምንቸቶች፥ መጫሪያዎቹን፥ ድስቶቹን፥ ሜንጦቹንና ማንደጃዎቹን ታደርጋለህ፤ ዕቃዎቹ ሁሉ ከነሐስ ሥራ።


አመዱንም ከመሠዊያው ላይ ያስወግዱ፥ ሐምራዊውንም መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤


አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃዎች ሁሉ መሸፈናቸውን በጨረሱ ጊዜ፥ ሰፈሩም ለመጓዝ ሲነሣ፥ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ከዚያም በኋላ ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። የቀዓት ልጆች የሚሸከሙአቸው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች እነዚህ ናቸው።


በእርሱም ላይ የአስቆጣውን ቁርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፥ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።