ዘኍል 35:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስኪሞት ድረስ በጥላቻ ገፍትሮ ቢጥለው፥ ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢጥልበት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ዐስቦበት ሌላውን በክፋት ገፍትሮ ቢጥለው ወይም እንዲሞት ሆነ ብሎ አንዳች ነገር ቢወረውርበት አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ሌላውን ሰው በጥላቻ ቢገፋው ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢወረውርበትና ይህ አድራጎቱ ሞትን ቢያስከትል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥል ቢጣላው፥ ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢጥልበት፥ ቢሞትም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪሞት ድረስ በጥላቻ ቢደፋው፥ ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢጥልበት፥ |
አማሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ሰይፍ መኖሩን ልብ ስላላለ ጥንቃቄ አላደረገም፤ ስለዚህ ኢዮአብ ሰይፉን ሆዱ ላይ ሻጠበት፤ አንጀቱም መሬት ላይ ተዘረገፈ፤ መድገምም አላስፈለገውም፥ አማሳይ በዚያው ሞተ። ከዚህ በኋላ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ፥ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ማሳደድ ጀመሩ።
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።
ወይም በጥላቻ እስኪሞት ድረስ በእጁ ቢመታው፥ የመታው ፈጽሞ ይገደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም ተበቃዩ ባገኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው።
እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው፤ የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ፤” አለው።
ሳኦልም፥ “ዳዊትን፥ ‘ንጉሡም ለልጅቱ ካንተ የሚፈልገው ጥሎሽ ጠላቶቹን ለመበቀል የመቶ ፍልስጥኤማውያንን ሸለፈት እንጂ ሌላ አይደለም ብላችሁ ንገሩት’ ” አላቸው። ሳኦል ይህን ያቀደው ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲወድቅ ነበር።
ከዚህ በኋላ ዳዊት በራማ ካለችው የራማዋ ከናዮት ሸሽቶ ወደ ዮናታን በመሄድ፥ “ምን አድርጌአለሁ? ምን በደልስ ፈጸምሁ? አባትህ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገውስ በፊቱ ምን ተገኝቶብኝ ነው?” ሲል ጠየቀው።
በዛሬው ዕለት በዋሻው ውስጥ ጌታ አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ላይ እንደጣለህ እነሆ በገዛ ዓይንህ አይተሃል፤ አንዳንዶች እንድገድልህ ገፋፍተውኝ ነበር፤ እኔ ግን፥ ‘ጌታ በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ በማለት ራራሁልህ።