እኛ ሁላችን መሞታችን አይቀሬ ነው፤ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር የተሰደደ ሰው በስደት በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።
ዘኍል 35:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስሕተት ነፍስ የገደለ ሁሉ እንዲሸሽበት እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸው ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም ስድስት ከተሞች ሳያስበው ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው እንዲሸሽባቸው ለእስራኤላውያን፣ ለመጻተኞችና በመካከላቸው ለሚኖር ለማንኛውም ሕዝብ የመማፀኛ ቦታዎች ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ለእስራኤላውያንና ለጊዜውም ሆነ ለዘለቄታው በእስራኤል ለሚኖሩ መጻተኞች የመማጠኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ ባለማወቅ ተሳስቶ ሰው የሚገድል ማንኛውም ግለሰብ ከእነርሱ ወደ አንዱ አምልጦ መጠጋት ይችላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባለማወቅ ነፍስ የገደለ ሁሉ ይሸሽባቸው ዘንድ እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች፥ በመካከላቸውም ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስሕተት ነፍስ የገደለ ይሸሽበት ዘንድ እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸው ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ። |
እኛ ሁላችን መሞታችን አይቀሬ ነው፤ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር የተሰደደ ሰው በስደት በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።