La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 34:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ጌታ ለዘጠኝ ነገድ ተኩል እንዲሰጥ ያዘዘው በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “ይህችን ምድር ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ደልድሉ፤ እግዚአብሔርም ለዘጠኙና ለግማሹ ነገድ እንድትሰጥ አዝዟል፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ለዘጠኝ ተኩል ነገዶች እንዲሰጥ እግዚአብሔር ያዘዘው በዕጣ የምትካፈሉት ርስት ይህ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ጠኙ ነገ​ድና ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ እንደ አዘዘ በዕጣ የም​ት​ወ​ር​ሱ​አት ምድር ይህች ናት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ እግዚአብሔር ለዘጠኝ ነገድ ተኩል ይሰጡአቸው ዘንድ ያዘዘ በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት፤

Ver Capítulo



ዘኍል 34:13
10 Referencias Cruzadas  

በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥


ርስት አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድሪቱ የተቀደሰውን ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ ጌታ ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ በዳርቻው ዙሪያ ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል።


ስለዚህ በጌታ ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፋፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ድንበሩም ወደ ዮርዳኖስ ይወርዳል፥ መጨረሻውም በጨው ባሕር ይሆናል። ምድራችሁ እንደ ድንበርዋ በዙሪያዋ ይህች ናት።”


በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር ይደርሳል።


እንግዲህ አሁን ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገድ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ ክፈለው።”