ከዚያም በኋላ ዘወትር የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የወር መባቻና፥ የተመረጡና የተቀደሱ የጌታ በዓላት ሁሉ መሥዋዕት፥ ሰውም ሁሉ ለጌታ በፈቃድ የሰጠውን ቁርባን አቀረቡ።
ዘኍል 28:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጠጥ ቁርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱ ወይፈን ጋራ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የሂን ግማሽ የወይን ጠጅ፣ ከአውራው በግ ጋራ የሂን አንድ ሦስተኛ፣ ከእያንዳንዱም የበግ ጠቦት ጋራ የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ ይቅረብ፤ ይህም በየወሩ መባቻ ዓመቱን ሙሉ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተገቢ ለሆነው የመጠጥ መባ ከእያንዳንዱ ኰርማ ጋር ሁለት ሊትር መጠጥ፥ ከአውራው በግ ጋር አንድ ተኩል ሊትር መጠጥ፥ ከእያንዳንዱም ጠቦት ጋር አንድ ሊትር የወይን ጠጅ አቅርቡ፤ በዓመቱ ሙሉ፥ ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ስለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት የተሰጠው የሥርዓት መመሪያ ይኸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። |
ከዚያም በኋላ ዘወትር የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የወር መባቻና፥ የተመረጡና የተቀደሱ የጌታ በዓላት ሁሉ መሥዋዕት፥ ሰውም ሁሉ ለጌታ በፈቃድ የሰጠውን ቁርባን አቀረቡ።
ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤ የወር መባቻ በዓላችሁን፤ ሰንበቶቻችሁን፤ ጉባኤያችሁንና በክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥ አልቻልሁም።
መስፍኑ በሰንበት ቀን ለጌታ የሚያቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸው ስድስት የበግ ጠቦቶችና ነውር የሌለበት አንድ አውራ በግ ይሁን፤
የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።
ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ።