ዘኍል 25:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፌጎር በመቅሠፍቱ ቀን ስለተገደለችው ስለ ምድያም አለቃ ልጅ ስለ እኅታቸው ስለ ከስቢ በፌጎር ምክንያት በሽንገላቸው ሸንግለዋችኋልና እነርሱን እንደ ጠላቶቻችሁ ቁጠሩአቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም ፌጎር ላይ በተፈጸመው ድርጊትና በፌጎር ምክንያት በመጣው መቅሠፍት በተገደለችው በምድያማዊው አለቃ ልጅ፣ በእኅታቸው በከስቢ አታልለው የጠላትነት ሥራ ስለ ሠሩባችሁ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የምታደርጉት እናንተን በፔዖር በማታለል ግፍ ስለ ሠሩባችሁና በፔዖር በወረደው መቅሠፍት ምክንያት በተገደለችው በአለቃቸው ልጅ በኮዝቢ አማካይነት በፈጸሙት ሽንገላ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ምድያም አለቃ ልጅ ስለ እኅታቸው ስለ ከስቢ በፌጎር ምክንያት በሸነገሉአችሁ ሽንገላ አስጨንቀዋችኋልና።” |
እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም ጥቂቶች ሰዎች ከእነርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ግብጽ ተጉዘው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም ለሀዳድ መሬትና አንድ መኖሪያ ቤት ሰጥቶ ምግብ ፈቀደለት።
ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ሊኖራችሁ ከሚገባ ቅንነትና ንጽሕና እንዳትርቁ ብዬ እፈራለሁ።
ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤ ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበለዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር አሉና።