La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 22:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታም መልአክ በለዓምን፦ “ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ” አለው። በለዓምም ከባላቅ ሹማምንት ጋር ሄደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔርም መልአክ በለዓምን፣ “መሄዱን ከሰዎቹ ጋራ ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው። ስለዚህ በለዓም ከባላቅ አለቆች ጋራ ሄደ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መልአኩ ግን “ከእነዚህ ሰዎች ጋር መሄዱን ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው፤ በዚህ ዐይነት በለዓም ከባላቅ ባለሥልጣኖች ጋር ሄደ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በለ​ዓ​ምን፥ “ከሰ​ዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ና​ገ​ር​ህን ቃል ብቻ ለመ​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ አለ​ቆች ጋር ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔርም መልአክ በለዓምን፦ ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ።

Ver Capítulo



ዘኍል 22:35
8 Referencias Cruzadas  

ሚክያስም፦ “በሕያው ጌታ እምላለሁ! አምላኬ የሚለውን እርሱን እናገራለሁ” አለ።


ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላዳመጠኝም።


በቅንነት የሚሄድ ይድናል፥ በጠማምነት የሚሄድ ግን ወዲያው ይወድቃል።


ባላቅም በለዓም እንደመጣ በሰማ ጊዜ በአርኖን ድንበር በድንበሩም ጨረሻ ወዳለችው ወደ ሞዓብ ከተማ ሊገናኘው ወጣ።


እኔ ግን በለዓምን መስማት አልፈለግሁም፤ እርሱም ፈጽሞ ባረካችሁ፥ እኔም ከእጁ አዳንኋችሁ።