ዘኍል 22:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አህያይቱም አይታኝ ከፊቴ ሦስት ጊዜ ፈቀቅ አለች፤ ከፊቴስ ፈቀቅ ባትል ኖሮ በእውነት አሁን አንተን በገደልሁህ፥ እርሷንም ባዳንኋት ነበር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አህያዪቱ አይታኝ ሦስቱንም ጊዜ ከፊቴ ዞር ባትልማ ኖሮ በእውነት እስካሁን አንተን በገደልሁህ፣ አህያዪቱን ግን በሕይወት በተውኋት ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንተ አህያ ግን እኔን በማየትዋ ሦስት ጊዜ ከፊቴ ሸሸች፤ አህያይቱ እንዲህ ባታደርግ ኖሮ አንተን ገድዬ እርስዋ በሕይወት እንድትኖር በተውኳት ነበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አህያዪቱም አይታኝ ከፊቴ ፈቀቅ አለች፤ ይህም ሦስተኛ ጊዜ ነው፤ ከፊቴስ ፈቀቅ ባላለች በእውነት አሁን አንተን በገደልሁህ፤ እርሷንም ባዳንኋት ነበር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አህያይቱም አይታኝ ከፊቴ ሦስት ጊዜ ፈቀቅ አለች፤ ከፊቴስ ፈቀቅ ባላለች በእውነት አሁን አንተን በገደልሁህ፥ እርስዋንም ባዳንኋት ነበር አለው። |
በለዓምም የጌታን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ ልትቃወመኝ መቆምክን አላወቅሁም፤ እንግዲህም ይህ አሁን በፊትህ ክፉ የሆነ ነገር ቢሆን እመለሳለሁ።”