La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 16:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተገታ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም በሕይወት ባሉትና በሞቱት መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተከለከለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህም መቅሠፍቱ እንዲቆም አደረገ፤ አሮንም በሞቱትና በሕይወት ባሉት መካከል ቆሞ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሙ​ታ​ንና በሕ​ያ​ዋን መካ​ከል ቆመ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ተከ​ለ​ከለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተከለከለ።

Ver Capítulo



ዘኍል 16:48
14 Referencias Cruzadas  

በዚያም ዳዊት ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት አቀረበ። ከዚያም ጌታ ለምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም መቅሰፍት ቆመ።


ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥ ቸነፈሩም ተወ፥


እያንዳንዳቸውም ጥናቸውን ወሰዱ፥ እሳትም አደረጉባቸው፥ ዕጣንም ጨመሩባቸው፥ ከሙሴና ከአሮንም ጋር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቆሙ።


እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጥቶ ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች በላቸው።


አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ጉባኤው መካከል ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፥ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው።


በቆሬም ምክንያት ከሞቱት ሌላ በመቅሠፍቱ የሞቱት ዐሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ አገኘውና “እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ፤” አለው።


እንዲሁም ከሚመጣው ቁጣ ያዳነንን ኢየሱስን፥ እርሱ ከሞት ያስነሣውን ልጁን፥ ከመንግሥተ ስማይ እንዴት እንደምትጠብቁ ይናገራሉ።


ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።