La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 16:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ምድሪቱ እኛንም ደግሞ እንዳትውጠን” ብለው በዙሪያቸው የነበሩ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ከእነርሱ ጩኸት የተነሣ ሸሹ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከጩኸታቸውም የተነሣ በአካባቢያቸው የነበሩት እስራኤላውያን ሁሉ፣ “ምድሪቱ እኛንም እኮ ልትውጠን ነው” ብለው ሸሹ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያ የነበሩት የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የእነዚያን ሰዎች ጩኸት በሰሙ ጊዜ ሸሹ፤ “ምድር እኛንም ልትውጠን ስለምትችል እንሩጥ!” እያሉም ጮኹ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዙ​ሪ​ያ​ቸው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከጩ​ኸ​ታ​ቸው የተ​ነሣ፥ “ምድ​ሪቱ እን​ዳ​ት​ው​ጠን” ብለው ሸሹ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዙሪያቸው የነበሩ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ከጩኸታቸው የተነሣ፦ ምድሪቱ እንዳትውጠን ብለው በረሩ።

Ver Capítulo



ዘኍል 16:34
6 Referencias Cruzadas  

ከፍጅት ድምፅ ሕዝቦች ሸሹ፤ በመነሣትህም መንግሥታት ተበተኑ።


የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ስለሚደርስ፥ በተራሮች መካከል ባለው ሸለቆ ትሸሻላችሁ። በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን በምድር መንቀጥቀጥ ምክንያት ከሆነው ሽሽት በበለጠ ትሸሻላችሁ። ከዚያም አምላኬ ጌታ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል።


እነርሱም የእነርሱም የሆነው ሁሉ በሕይወታቸው ሳሉ ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ላይ ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ።


እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጥቶ ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች በላቸው።