La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 9:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልጆቹም ገብተው ምድሪቷን ወረሱ፤ የምድሪቱን ሰዎች ከነዓናውያንን በፊታቸው ደመሰስካቸው፥ የወደዱትን ነገር እንዲያደረጉባቸው ከነገሥታቶቻቸውና ከምድሪቱ ሕዝቦች ጋር በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በምድሪቱ ወንዶች ልጆቻቸው ገቡባት፤ ወረሷትም። በምድሪቱ ላይ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያን በፊታቸው አንበረከክህ፤ ያሻቸውን ያደርጉባቸው ዘንድ ከነዓናውያንን ከንጉሦቻቸውና ከምድሪቱ ሕዝቦች ጋራ በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልጆቻቸው የከነዓንን ምድር ድል አድርገው ያዙ፤ በዚያ ይኖሩ የነበሩትንም ሕዝብ በፊታቸው ሆነህ አንተ ድል ነሣህላቸው፤ በነገሥታትና በዚያች የከነዓን አገር ሕዝብ ላይ የፈለጉትን ሁሉ ያደርጉባቸው ዘንድ ኀይልን ሰጠሃቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ነ​ዓን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች በፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ሃ​ቸው፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ት​ንም ነገር ያደ​ር​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ር​ሱ​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ የም​ድ​ሩ​ንም አሕ​ዛብ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ልጆቹም ገብተው ምድሩን ወረሱ፥ የምድሩን ሰዎች ከነዓናውያንን በፊታቸው አዋረድህ፥ የሚወድዱትንም ነገር ያደረጉባቸው ዘንድ እነርሱንና ነገሥታቶቻቸውን የምድሩንም አሕዛብ በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።

Ver Capítulo



ነህምያ 9:24
13 Referencias Cruzadas  

“አምላካችሁ ጌታ ከእናንተ ጋር አይደለምን? በምድርም የሚቀመጡትን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ምድርም በጌታና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለችና በዙሪያችሁ ሁሉ ዕረፍትን ሰጥቶአችኋል።


ነገር ግን ምርኮኛ ይሆናሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን እነርሱን ወደ ምድሪቱ አስገባቸዋለሁ፥ እናንተም የናቃችኋትን ምድር ያውቋታል።


እንዲሁም ፈቃዱን ለመፈጸም ታስረው ከተያዙበት ከዲያብሎስ ወጥመድ ወጥተው ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ ያደርጋቸዋልና።


እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ተራራማውን አገር ደቡቡንም ቈላውንም የተዳፋቱንም ስፍራ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዳዘዘውም እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


ጌታም ለሙሴ እንደ ተናገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደየነገዳቸው ድርሻ ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።


የዔግሎም ንጉሥ፥ የጌዝር ንጉሥ፥


የቲርሳ ንጉሥ፥ ነገሥታቱ ሁሉ ሠላሳ አንድ ናቸው።


የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፥ በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ እነርሱም የምድሪቱ ገዢዎች ሆኑ።


ጌታም ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።


ጌታ ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።


በዚያች ዕለት እግዚአብሐር የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢስን በእስራኤላውያን ፊት እንዲሸነፍ አደረገው።