ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው፤
ነህምያ 7:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ ገዛ ከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምርኮኞች ብዙዎቹ ከባቢሎን አውራጃዎች ተነሥተው፥ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ምድር በመመለስ፥ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ከተማው ገብቶአል፤ ናቡከደነፆር ከወሰዳቸው ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በባቢሎን ምድር ይኖሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። |
ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው፤
ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁ አምላክ ቤትም እንደ ሄድን በንጉሡ ዘንድ ይታወቅ፥ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፥ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፥ ያም ሥራ በጥንቃቄ ይሠራል፥ በእጃቸውም ይከናወናል።
እነርሱም፦ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ትሩፋን በታላቅ መከራና በመሰደብ ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከዓዛርያ፥ ከራዓምያ፥ ከናሐማኒ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከቢልሻን፥ ከሚስፌሬት፥ ከቢግዋይ፥ ከኔሑም፥ ከባዓና ጋር የመጡ የእስራኤል ሕዝብ የሰዎች ቍጥር ይህ ነው።