ነህምያ 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገባቸውም የሐሩማፍ ልጅ ዬዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። በአጠገቡም የሐሻቤኔያ ልጅ ሐጡሽ አደሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤርማፍ ልጅ ይዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ፤ የአሰበንያ ልጅ ሐጡስ ደግሞ ከርሱ ቀጥሎ ያለውን መልሶ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐሩማፍ ልጅ የዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት የሚገኘውን ክፍል ሠራ። ቀጥሎ ያለውንም ክፍል የሐሻበንያ ልጅ ሐቱሽ ሠራው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገባቸውም የኤርማፍ ልጅ ይዳያ በቤቱ አንጻር ያለውን ሠራ። በአጠገቡም የአሰብንብሔም ልጅ ሐጡስ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገባቸውም የኤርማፍ ልጅ ይዳያ በቤቱ አንጻር ያለውን አደሰ። በአጠገቡም የአሰበንያ ልጅ ሐጡስ አደሰ። |
ከእነርሱም በኋላ ብንያምና ሐሹብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን አደሱ። ከእነርሱም በኋላ የአናንያ ልጅ የማዓሤያ ልጅ አዛርያ በቤቱ አጠገብ ያለውን አደሰ።
ሌዋውያኑ ኢያሱ፥ ቃድምኤል፥ ባኒ፥ ሐሻብንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሽባንያ፥ ፕታሕያ እንዲህ አሉ፦ “ቁሙ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ጌታ አምላካችሁን ባርኩ። ከበረከትና ከምስጋና ሁሉ በላይ ከፍ ያለው የክብርህን ስም ይባርኩ።