ነህምያ 11:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች የተወሰኑት በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፦ ከፋሬስ ልጆች የማሃላልኤል ልጅ፥ የሽፋጥያ ልጅ፥ የአማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዑዚያ ልጅ ዓታያ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከይሁዳና ከብንያም ወገን የሆኑት የተቀሩት ሰዎች ደግሞ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከይሁዳ ዘሮች፦ ከፋሬስ ዘር የመላልኤል ልጅ፣ የሰፋጥያስ ልጅ፣ የአማርያ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የዖዝያ ልጅ አታያ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ነገድ አባላት፦ የዘካርያስ የልጅ ልጅ የሆነው የዑዚያ ልጅ ዐታያ፤ ሌሎች የቀድሞ አያቶቹ የይሁዳ ልጅ የሆነው የፋሬስ ዘሮች የሆኑትን አማርያን፥ ሸፋጥያንና ማሀላልኤልን ይጨምራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፤ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ፥ የሰፋጥያስ ልጅ፥ የሰማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዖዝያ ልጅ አታያ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፥ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ የአማርያ ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዖዝያ ልጅ አታያ፥ |
በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃው መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዱ በየርስቱና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ኖሩ።