በለምለሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ያያት ሁሉ እጁን ሰዶ ይበላታል።
ናሆም 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሽግሽ ሁሉ የመጀመሪያውን የበሰለ ፍሬ እንደ ያዙ እንደ በለስ ዛፎች ነው፤ በሚወዛወዙ ጊዜ በሚበላው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሽጎችሽ ሁሉ ሊበሉ እንደ ደረሱ የበኵራት በለስ ፍሬ ናቸው፤ በሚወዛወዙበት ጊዜ፣ ፍሬዎቹ በበላተኛው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምሽግሽ ሁሉ ቀድሞ የደረሰ ፍሬ እንደ ተሸከመ የበለስ ዛፍ ይሆናል፤ እርሱ ተነቅንቆ ፍሬው በተራገፈ ጊዜ በበላተኛ አፍ ውስጥ ይወድቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምባሽ ሁሉ የመጀመሪያውን የበሰለ ፍሬ እንደ ያዙ እንደ በለስ ዛፎች ነው፣ ቢወዛወዝ በሚበላው አፍ ውስጥ ይወድቃል። |
በለምለሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ያያት ሁሉ እጁን ሰዶ ይበላታል።
በአንደኛው ቅርጫት አስቀድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፤ በሁለተኛውም ቅርጫት ከክፋቱ የተነሣ ሊበላ የማይችል እጅግ ክፉ በለስ ነበረበት።