La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 27:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ተፉበት፤ መቃውንም ነጥቀው ራሱን መቱት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ተፉበትም፤ የሸንበቆ በትሩን ከእጁ ወስደው ራሱን መቱት፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምራቃቸውንም ይተፉበት ነበር፤ ዘንጉንም ከእጁ ወስደው ራስ ራሱን ይመቱት ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ተፉበትም፤ መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 27:30
12 Referencias Cruzadas  

የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ ጌታ፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው፥ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ታማኙ ስለ ጌታ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።’


ጀርባዬን ለገራፊዎች፥ ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ፤ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።


ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቁሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤


የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው፥ ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚያዞርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።


ተጨነቀ፥ ተሰቀየም፥ አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።


አንቺ ግን ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትንሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


በዚያን ጊዜ ፊቱ ላይ ተፉበት፥ መቱት፥ በጥፊም መቱት


ያፌዙበታል፤ ይተፉበታል፥ ይገርፉታል፥ ከዚያም ይገድሉታል፤ እርሱ ግን ከሦስት ቀን በኋላ ይነሣል።”


በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ይተፉበት ጀመር፤ ዐይኑንም ሸፍነው በጡጫ እየመቱት፥ “እስቲ ትንቢት ተናገር” ይሉት ነበር። ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።


ራሱንም በበትር መቱት፤ ተፉበትም፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት።