ማቴዎስ 25:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝም፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ አልጠየቃችሁኝም።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝም፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ አልጠየቃችሁኝም።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዳ ሆኜ መጥቼ ነበር፥ አልተቀበላችሁኝም፤ በቤታችሁ ታርዤ ነበር፥ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ ነበር፥ አልጠየቃችሁኝም፤’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፤ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና። |
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸዋልም አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ ስለ ክፉ ሥራችሁ እጐበኛችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።
እነርሱም እንዲህ ሲሉ ይመልሱለታል ‘ጌታ ሆይ! ተርበህ ወይም ተጠምተህ ወይም እንግዳ ሆነህ ወይም ታርዘህ ወይም ታመህ ወይም ታስረህ መቼ አየንህና አላገለገልንህም?’
ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ፤” አለው።