ማቴዎስ 24:51 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሁለት ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይቈራርጠዋል፤ ዕድል ፈንታውንም ከግብዞች ጋራ ያደርግበታል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያንን አገልጋይ ጌታው ይቀጣዋል፤ ዕጣ ክፍሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። |
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ አምላክ የሌላቸው በፍርሃት ራዱ፤ “ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ? ለዘለዓለምም ከምትነድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ?”
አብርሃምን፥ ይስሐቅንና ያዕቆብን፥ ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት እያያችሁ፥ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ፥ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።