ማቴዎስ 13:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም በነቢዩ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፤ “አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ፤” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም በነቢዩ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፤ “አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነበት ምክንያት በነቢይ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው፦ “ንግግሬን በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውን እናገራለሁ።” |
እንዲህ ተብሎ የተነገረው የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል። መስማትን ትሰማላችሁ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ ነገር ግን አትመለከቱም።
አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፥ የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።
ነገር ግን፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር ተሰውሮም የነበረውን እንናገራለን።
ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁን ግን የለም፤ ከጥልቁም ሊወጣ ነው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ የምድር ኗሪዎች አውሬው አስቀድሞ እንደ ነበረ አሁን ደግሞ እንደሌለ፥ ነገር ግን ተመልሶ እንደሚመጣ ሲያዩ ይደነቃሉ።