ማርቆስ 5:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ወደ ጀልባዪቱ በሚገባበት ጊዜ፥ በአጋንንት ተይዞ የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር አብሮት ለመሆን ለመነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ወደ ጀልባዪቱ በሚገባበት ጊዜ፣ አጋንንት ዐድረውበት የነበረው ሰው ዐብሮት ለመሆን ለመነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ጀልባው በመግባት ላይ ሳለ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው፦ “እባክህ ልከተልህ!” ብሎ ለመነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ታንኳይቱም በገባ ጊዜ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲኖር ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ታንኳይቱም በገባ ጊዜ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲኖር ለመነው። |
ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ወደ ኢየሱስም በመጡ ጊዜ፥ የአጋንንት ሠራዊት አድረውበት የነበረው ሰው፥ ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ተቀምጦ አዩት፤ ፍርሃትም አደረባቸው።