ማርቆስ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስን፥ “ወደ አሣማዎቹ እንድንገባ ስደደን፤” ብለው ለመኑት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርኩሳን መናፍስቱም ኢየሱስን፣ “ወደ ዐሣማዎቹ ስደደን፤ እንድንገባባቸውም ፍቀድልን” ብለው ለመኑት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ “እባክህ ሄደን ወደ ዐሣማዎቹ እንድንገባ ፍቀድልን፤” ብለው ለመኑት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወደ እሪያዎቹ እንድንገባ ስደደን፤” ብለው ለመኑት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እሪያዎቹ እንድንገባ ስደደን ብለው ለመኑት። |
ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
እርሱም ፈቀደላቸው። ርኩሳን መናፍስቱም ወጥተው በዐሣማዎቹ ገቡ፤ ሁለት ሺህ ያህል ዐሣማዎችም በርግገው ከገደሉ አፋፍ ወደ ባሕሩ ተወረወሩ፤ በባሕሩ ውስጥም ሰጠሙ።