ማርቆስ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እጁ የሰለለችውን ሰው “ተነሥ! በመካከል ቁም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እጁ የሰለለችበትን ሰው፣ “ተነሥተህ መካከል ላይ ቁም” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እጀ ሽባውን ሰው፦ “ና በመካከል ቁም” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጁ የሰለለችውንም ሰው “ተነሥተህ ወደ መካከል ና፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጁ የሰለለችውንም ሰው፦ ተነሥተህ ወደ መካከል ና አለው። |
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።
እንግዲህ ክርስቶስ በሥጋ ስለ እኛ መከራን በመቀበሉ፥ እናንተም በዚህ ሐሳብ ራሳችሁን አስታጥቁ፤ ምክንያቱም በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአል።