ማርቆስ 1:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ለሰውየው በመራራት እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፥ “እፈቅዳለሁ፥ ንጻ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ለሰውየው በመራራት እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ!” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ራራለትና እጁን ዘርግቶ እየዳሰሰው፥ “ፈቅጃለሁ፤ ንጻ!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወድዳለሁ፤ ንጻ፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወድዳለሁ፤ ንጻ አለው። |
ኢየሱስ ከጀልባዋ በሚወርድበት ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ አየ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለነበሩም አዘነላቸው፤ ብዙ ነገርም ያስተምራቸው ጀመር።
ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።