Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እኛ ያለን ሊቀ ካህናት በድካማችን ሊራራልን የሚችል ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር እንደ እኛ ተፈተነ፤ ሆኖም ምንም ኃጢአት አልሠራም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እኛ ያለን የካህናት አለቃ በድካማችን ሊራራልን የሚችል ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር እንደ እኛ ተፈተነ፤ ሆኖም ምንም ኃጢአት አልሠራም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሊቀ ካህ​ና​ታ​ችን ለድ​ካ​ማ​ችን መከራ መቀ​በ​ልን የማ​ይ​ችል አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን ከብ​ቻዋ ከኀ​ጢ​አት በቀር እኛን በመ​ሰ​ለ​በት ሁሉ የተ​ፈ​ተነ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 4:15
20 Referencias Cruzadas  

እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን ስለ እኛ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ኃጢአት አደረገው።


ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።


እርሱ ኃጢአት አላደረገም፤ በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም፤


እንዲህ ያለው ቅዱስ፥ ነቀፋ የሌለበት፥ ንጹሕ፥ ከኃጢአተኞች የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት ሊኖረን ይገባል፤


እንግዲህ በሰማያት የወጣ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።


እርሱ ራሱም ደግሞ ድካምን ስለሚለብስ፥ ላልተማሩትና ለሚሳሳቱት ሊራራላቸው ይችላል፤


ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነት የምናገር ከሆንሁ እናንተ ስለምን አታምኑኝም?


አሟሟቱን ከክፉዎችም ጋር፥ መቃብሩን ከባለጠጎችም ጋር አደረጉ፤ ግፍ ግን አላደረገም ነበር፤ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።


እናንተ በመከራዬ ከእኔ ጋር ጸንታችሁ የኖራችሁ ናችሁ፤


ለአርባ ቀን በዲያብሎስ ተፈተነ። በእነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፤ ቀኖቹም በተፈጸሙ ጊዜ ተራበ።


ኤፍሬም ሆይ! እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ጲቦይም እመለከትሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።


መጻተኛውን አትጨቁን፤ እናንተ ራሳችሁ በግብጽ ምድር መጻተኞች ስለ ነበራችሁ የመጻተኛ ነፍስ እንዴት እንደ ሆነች ታውቃላችሁና።


ፍርድን ወደ ድል እስኪያመጣ ድረስ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆን አይሰብርም፤ የሚጤስን የጧፍ ክር አያጠፋም።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በዲያብሎስ እንዲፈተን መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው።


ሕግ ከሥጋ ድካም የተነሣ ማድረግ ያልቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌና ስለ ኃጢአት ልኮ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ፤


እንዲሁም ክርስቶስ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ሲታይ ሊያድናቸው ለሚጠባበቁት ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን መዳንን ለማምጣት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios